አገልግሎቶቻችን
የእድሩ አባል ለመሆን
የኢትዮጵያኖች የመረዳጃ እድር አባል ለመሆን የሚያስፈልገው በኔዘርላንድስ ውስጥ ነዋሪ የሆነ፣ ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም የእድሩን ሕገ ደንብ የተቀበለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዪጵያዊ የእድሩ አባል መሆን ይችላል።
የእድሩ አባል ለመሆን የአባልነት መመዝገቢያ የምንጠይቅ ሲሆን የመመዝገቢያው ተመን €100 ነው ይህም በአንዴ የሚከፈል ሲሆን የወራዊ ክፍያው ደግሞ €5 ነው። የወርሃዊ ክፍያውን በየወሩ፣ የወሩ ማገባደጃ ላይ በቀጥታ ዴቢት (automatische incasso) ከባንኮ ላይ ይቆረጣል፣ በአንድ ጊዜ የአመቱን ክፍያ ማድርግም ይቻላል።
በቀጥታ መክፈል ከፍለጉ ከዚህ ወረድ ብሎ በተቀመጠው የባንክ ቁጥር ማስተላለፍ ይችላሉ
Vereniging I.D.I.R Holland
NL35 INGB 0104 0999 84
አባል ለመሆን ከፈለጉ ከእዚህ ግርጌ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው መመዝገቢ አንቀጹን ይምሉ
ስለ ክፍያ
የቀብር ሥነ ስርዓትን በተመለከት የእድሩ አባል ወይንም ቤተሰቡ በሚፈልገው መንገድ ከእድሩ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ጋር ተወያይቶ የቀብር ሥነ ስረዓቱ እንዲፈጸም የማድረግ መት አለው። የወጪውም ተመን በእድሩ መስተዳደሪያ ደንብ "አንቀጽ 2.2.10" መሰረት የተወሰነ ሲሆን ይህ የገንዘብ ተመን የቀብር ዋስትና ያለውም የሌለውም የእድሩ አባል በሞት አደጋ ጊዜ ከእድሩ የሚያገኘው ገንዘብ አንድ ዓይነት ነው ።
ነገር ግን አንድ አባል በአባልነት ተመዝግቦ ሙሉ ዓመት (12 ወራት) ካልሞላው የገንዘብ ጥቅም አያገኝም።
የግል ሁኔታዎች
ለረጅም ጊዜ የእድሩ አባል ሆነው እና የአባልነት ክፍያዎትን እያሟሉ ኑሮዎትን በሌላ ሃገር ቢያደርጉ ለስራ አስፈጻሚ ቦርድ የኑሮ ሁኔታዎትን አስረድተው አባልነቶትን የመቀጠል መብት ይኖሮታል።