ስለ እኛ

 

የኢትዮጵያውያኖች የመረዳጃ እድር በኔዘርላንድስ እ.ኤ.አ. በ2022 የተመሰረተው ኑሮዋቸውን በኔዘርላንድ አገር ባደረጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ሲሆን የተመሰረተበትም ዓላማ ኢትዮጵያውያኑ የእድሩ አባል ወይንም የእድር አባል ቤተሰብ ማለትም እድሜው ከ18 አመት በታች የሆነ ልጅ በሞት ሲለይ ለቀብር ስነ ስርዓት ማገዣ ወይም ለአስከሬን ወደ ትውልድ ቦታ መላኪያ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ የተቋቋመ ሲሆን

እንዲሁም ከእዚህ በታች የተጠቀሱትን ማህበራው ጉዳዮችም በሙሉ አካቶ እየትንቀሳቀሰ ይገኛል

 

  • መረጃ መስጠት
  • መረዳዳት 
  • መጠያየቅ
  • አባላት ሲታመሙ መጠየቅ
  • ማህበራዊ ሕይወትን ለማጠናከር በአመት አንድ ጊዜ የአባላት ቀን ይዘጋጃል 

የኢትዮጵያውያኖች የመረዳጃ እድር በኔዘርላንድስ የራሱ የሆነ የመተዳደሪያ ሕግ እና ደንብ ያለው ሲሆን በኔዘርላንድ የንግድ ምክር ቤት ተመዝግቦ ከህግ የሚጠበቅበትን ግዳጆች አሟልቶ እና አስጠብቆ የሚንቀሳቅስ የኢትዮጵያውያን ማህበረስብ የእድሩ አባላት የጋራ ንብረት ነው።

 

የበለጠ የእድሩን ሕገ ደንብ ለመረዳት ከዚህ ግርጌ ያለውን የማውርጃ  አዝራር ይጠቀሙ

 

የኢትዮጵያውያኖች የመረዳጃ እድር በኔዘርላንድስ ሕገ ደንብ Pdf
PDF – 186,1 KB 32 downloads